ቼልሲ እና ቶተንሀም ድል ሲቀናቸው ሊቨርፑል ተሸንፏል ።
ቼልሲ እና ቶተንሀም ድል ሲቀናቸው ሊቨርፑል ተሸንፏል ።
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ሌስተር ሲቲን ፣ ቶተንሀም ደግሞ ኖቲንግሃም ፎረስትን በተመሳሳይ ውጤት 3ለ1 ሲያሸንፉ ሊቨርፑል በቦርንማውዝ 1 ለ 0 ተረቷል ።
ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የማሸነፊያ ግቦች ቼልዌል ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ኮቫኪች ሲያስቆጥሩ ሌስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ደግሞ ዳካ አስቆጥሯል።
የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ደግሞ ሀሪ ኬን 2 ጎል እና ሰን ሁንግ ሚን ሲያስቆጥሩ የኖቲንግሀም ፎረስትን ብቸኛ ግብ ዎራል አስቆጥሯል።
ቦርንማውዝ ሊቨርፑልን እንዲያሸንፍ ያደረገች ግብ ደግሞ ቢሊንግ አስቆጥሯል ።
ሌላ በሊጉ የተደረጉ መርሐ ግብሮች
ሊድስ 2 – 2 ብራይተን
ኤቨርተን 1 – 0 ብሬንትፎርድን