ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናክሯል
በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በአስራ ስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን ጋር 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ፍሪምፖንግ ሜንሱ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ሲያስቆጥሩ የኢትዮጵያ መድንን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ሲሞን ፒተር ሲሞን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ 1ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ኢትዮጵያ መድን በበኩላቸው ደግሞ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምስት ነጥብ ዝቅ ብለው 2ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ አርባምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።
በዕለቱ በተደረገ ሌላ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 ረቷል ።
ሲዳማ ቡና 0 – 2 ድሬደዋ ከተማ
⚽️ 2′ ያሬድ ታደሰ
⚽️ 86′ አቤል አሰበ