የለንደኖቹ ክለቦች አርሰናል እና ቼልሲ ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል ።

በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መሪው አርሰናል ከ በርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ድል የራቀው ቼልሲ ደግሞ ሊድስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

የመድፈኞቹ አርሰናሎችን የማሸነፊያ ግቦች ቶማስ ፓርቴ ፣ ኔልሰን እና ዋይት ሲያስቆጥሩ በርንማውዝን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ደግሞ ቢሊንግ እና ሰነሲ ከመረብ አሳርፈዋል ።

አርሰናል 2 ለ 0 ከመመራት ተነስተው ነው ቦርንማውዝን 3 ለ 2 መርታት የቻሉት

የአርሰናሉ ኔልሰን ተቀይሮ ገብቶ 90+7 ላይ የአርናልን 3ኛ ግብ ማስቆጠሩ የአርሰናልን ድል ጣፋጭ እንዲሆን አስችሎታል ።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ደግሞ ተከላካዩ ፎፋና ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ፉልሀም እንዲሁም ቼልሲ ከሌስተር ሲቲ የሚገናኙ ይሆናል።

ሌሎች በተመሳሳይ ሰዓት የተደረጉ መርሀግብሮች

አስቶንቪላ 1 – 0 ክሪስታል ፓላስ
ብራይተን 4 – 0 ዌስትሀም
ወልቭስ 1 – 0 ቶተንሀም

Leave a Reply

Your email address will not be published.