ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ሪከርድ ሰበረ !

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ሪከርድ ሰበረ !

በ2023ቱ የፈረንሳይ ሃውትስ ደ ፍራንስ ፓስ ዴ ካላስ ሊቪን አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር
ለሜቻ ግርማ ክብረወሰኑን በማሻሻል አሸንፏል ።

በ3000 ሜትር ወንዶች በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ 7:23:81 በመግባት ክብረወሰኑን ሲያሻሻል በውድድሩ ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጥላሁን ሀይሌ 6ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል ።

በ1500 ሜ ሴቶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ1ኛእስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ሲጨርሱ
ጉዳፍ ፀጋዬ 3:49:58 በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች ።

አትሌት ሒሩት መሸሻ ፣ አትሌት ፍሬወይኒ እና አትሌት አክሱማይት 2 እስከ 4 በመውጣት ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

.

Leave a Reply

Your email address will not be published.