ተጠባቂው የሸገር ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ግብ መሀመድ ናስር ከመረብ አሳርፎ ቡናማዎቹን መሪ ቢያደርግም የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ቸርነት ጉግሳ አስቆጥሮ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀያ ስድስት ነጥብ ሰብስቦ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ ቡና በአስራ ስምንት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ መቻል የሚገናኙ ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.