በለንደን ደርቢ ቶተንሀም ድል ቀንቶታል
በኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሀግብር የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከፉልሀም ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።
የቶተንሀምን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሀሪ ኬን ከመረብ ማሳረፍ አሳርፏል ።
ቶተንሀም በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ስድስት ነጥቦች በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፉልሀም በሰላሳ አንድ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል ።
በቀጣይ በሊጉ መርሐግብር ቶተንሀም ከማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ፉልሀም ከ ቼልሲ የሚገናኙ ይሆናል።
ፉልሀም 0 – 1 ቶትነሀም
⚽️ ኬን 45+1′
