በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዌስትሀም ሲያሸንፍ ሌስተር ሲቲ እና ብራይተን ነጥብ ተጋርተዋል ።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጥር 13 ቀን የተደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ዌስትሀም ሲያሸነፉ ሌስተር ሲቲ እና ብራይተን ነጥብ ተጋርተዋል ።

ዋስትሀም በለንደን ስታዲየም ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የዌስትሀምን የማሸነፊያ ግቦቹን ጃሮድ ቦውን አስቀምጧል ጥሯል።

ሌስተር ሲቲ በኪንግ ፓወር ስታዲየም ከብራይተን ጋር ባከናወነው ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል ።

የሌስተርን ግቦች ኦልብራይተን እና ባርንስ ሲያስቆጥሩ የብራይተንን የአቻነት ግቦች ሚቶማ እና ፈርጉሰን ከመረብ አሳርፈዋል ።

በሌላ ጨዋታ አስቶንቪላ ሳውዛምፕተንን በዋትኪንስ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ኤቨርተን እና ሳውዛምፕተን መሸነፋቸውን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በእኩል አስራ አምስት ነጥብ አስራ ዘጠነኛ እና ሀያኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.