ማንችስተር ዩናይትድና ክሪስትያል ፓላስ ነጥብ ተጋሩ
ማንችስተር ዩናይትድና ክሪስትያል ፓላስ ነጥብ ተጋሩ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ክሪስትያል ፓላስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል ።
የማንችስተር ዩናይትድን ግብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀ 44′ ተኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የክሪስትያል ፓላስን የአቻነት ግብ ኦሊሴ 90+1 ላይ አስቆጥሯል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ካሴሚሮ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቀጣይ ክለቡ ከአርሰናል ጋር የሚያደርገው የሊግ ጨዋታ ላይ አይሰለፍም።
ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ያጠበበ ሲሆን በሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃውን አስከብሯል።
👉በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል እንዲሁም ክሪስቲያል ፓላስ ከኒውካስል ዩናይትድ ይጋጠማሉ ።