መድፈኞቹ በለንደን ደርቢ ቶተንሃምን ድል አድርገዋል

በ20ኛው ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር በለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃምን ረትቷል ።

ለመድፈኞቹ የማሸነፊያውን ግቦች ኦዴጋርድ እና ሁጎ ሎሪስ በራሱ ላይ አስቆጥረው ነው የለንደን ደርቢን መርታት የቻሉት ።

አርሰናል ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት በማስፋት በአርባ ሰባት ነጥብ መሪነቱን ያጠናከረ ሲሆን ቶተንሀሞች ደግሞ በበኩላቸው ሰላሳ ሶስት ነጥብ በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አርሰናል ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚጫወቱ ሲሆን ቶተንሀም በተስተካካይ ጨዋታ ከ ማንችስተር ሲቲ የሚገናኙ ይሆናል ።

ቶተንሀም 0 – 2 አርሰናል

                        ⚽ ሁጎ ሎሪስ (በራስ ላይ)
⚽ ኦዴጋርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.