የሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች ታውቀዋል።

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች ታውቀዋል።

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ዙር ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ደግሞ የአንድ ሳምንት ጨዋታዎች የቀራቸው ሲሆን ለሁለተኛው ዙር ውድድር ቡድኖች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚደረግባቸው ቦታዎች ተገልፀዋል።

በዚህም መሰረት በሀዋሳ ሲካሄድ የቆየው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር በባህር ዳር የሚደረግ ሲሆን ሰበታ ሲካሄድ የቆየው የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ እና የዝውውርና የውድድር መጀመርያ ጊዜ በቅርቡ እንደሚገለፅ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

ምንጭ 👉የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published.