አትሌት ሰለሞን ባረጋ ድል አድርጓል !
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ድል አድርጓል
በስፔን ኤልጎይባር በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የአገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያዊያኖቹ እና ኤርትራዊያን ደምቀው አምሽተዋል ።
በወንዶች 10 ኪሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አስደናቂ በ33:14 ደቂቃ አሸናፊ ሲሆን በትውልድ ኢትዮጵያዊው በዜግነት ባህሬን የሆነው ብርሀን ባለው ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል።
በሴቶች የ10 ኪሜ ውድድር ደግሞ ኤርትራዊቷ አትሌት ራሄል ዳንኤል አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፋለች ።