አርሰናል በድንቅ ጨዋታና በማራኪ ጎሎች ዌስትሀምን አሸነፈ ።

የ17ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሰኞ መስከረም 17 ቀን ምሽት 5.00 የተጀመረ ጨዋታ ሲጠናቀቅ በመጀመሪያው 45
በሰይድ ቤንራህማ በፍፁም ቅጣት ምት በተቆጠረበት ግብ 1ለ0 የተመራው አርሰናል ከረፍት መልስ በፍጹም የበላይነት በማራኪ ጨዋታ
በቡካዮ ሳካ ፣ ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ኤዲ ኒኪታህ ድንቅ ጎሎች ዌስትሀምን 3ለ1 አሸንፏል ።

👉 አርሰናል 3 – 1 ዌስትሀም

⚽ 53’ሳካ           ⚽ 27’ቤንርሀማ ፍ.ቅ.ም
⚽ 58’ማርቲኔሊ
⚽69′ ኒኪታህ

አርሰናል 15 ጨዋታዎች አከናውኖ በ40 ነጥብ
ሊጉን ሲመራ ኒውካስል 16 ጨዋታዎች አከናውኖ በ33 ነጥብ ሁለተኛ ላይ ሲቀመጥ
ማንቸስተር ሲቲ 14 ጨዋታዎችን ተጫውቶ በ32 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

👉በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ብራይተን እንዲሁም ዌስትሀም ከብሬንትፎርድ የሚገናኙ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.