የዓለም ዋንጫ ባልተፈቀደለት ቱርካዊ የመነካቱ ጉዳይ ፊፋን አስቆጥቷል ምርመራ እየተደረገ ነው

የዓለም ዋንጫ ባልተፈቀደለት ሰው የመነካቱን ጉዳይ ፊፋ ሊመረምር ነው

ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አንድ የታዋቂ ሰዎች ምግብ አብሳይ ዋንጫውን ይዞ የመታየቱን ጉዳይ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በመመርመር ላይ መሆኑን አስታወቋል።

ታዋቂው ቱርካዊ ምግብ አብሳይ ኑስረት ጉክቸ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በሚታወቅበት ስሙ ‘ሳልት ቤ’ ባለፈው እሁድ ከፍጻሜ ጨዋታው በኋላ እንዴት ወደ ሜዳው እንደገባና ዋንጫውን ለመያዝ እንደበቃ ምርመራ ይደረጋል ሲል ፊፋ አስታውቋል።

በፊፋ ድህረ ገጹ እንዳሰፈረው ዋንጫው መነካት የሚችለው በተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሲሆን እነሱም የቀድሞ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎች እና የአገራት መሪዎች መንካት ከሚፈቀድላቸው ጥቂቶቹ ናቸው።

ቱርክ፣ ኢስታንቡል ውስጥ በትንሽ ልኳንዳ ሥራ የጀመረው የ 39 ዓመቱ ‘ሳልት ቤ’ሳልት ቤ፣ አሁን ከ 20 በላይ ቅንጡ ምግብ ቤቶች በዓለም ዙሪያ ያሉት ሲሆን 70 ሚሊዮን ዶላር ሃብት እንዳለው ይነገራል።

በዚህም የአለም ዋንጫ ምክንያት እጅግ በርካታ አድናቂዎችን ለማፍራትና እራሱንና ድርጅቱን ለማስተዋወቅ ተጠቅሞበታል ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.