የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ ለሚያደርገው ተሳትፎ ዝግጅት የተጫዋቾች ቁጥር ወደ 28 ተቀንሶ ለተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም 42 ተጫዋቾችን ያካተተ ጊዜያዊ የተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በድሬዳዋ እየተካሄደ በሚገኘው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ ተገኝተው የተጫዋቾችን ወቅታዊ ብቃት እና ሁኔታ በመገምገም የተጫዋቾችን ቁጥር ወደ 28 በመቀነስ ጥሪ አድርገዋል።

ከታች ስማቸው የተጠቀሱ ተጫዋቾችም ታህሳስ 18 ቀን 2015 ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል። በቀጣዩ ቀን የጤና እና አካል ብቃት ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላም ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናል።

28 ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች
ፋሲል ገ/ሚካኤል ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡና
ባህሩ ነጋሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ተከላካዮች
ሱሌማን ሀሚድ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው ፋሲል ከነማ
ጊት ጋትኩት ሲዳማ ቡና
አስቻለው ታመነ ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብርሃኑ በቀለ ሃዲያ ሆሳዕና
ፈቱዲን ጀማል ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ ኢትዮጵያ ቡና
ሚልዮን ሰለሞን አዳማ ከተማ
አማካዮች
ጋቶች ፓኖም ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው ፋሲል ከነማ
ከነዓን ማርክነህ መቻል
መስኡድ መሐመድ አዳማ ከተማ
ታፈሰ ሰለሞን ፋሲል ከነማ
ፉአድ ፈረጃ ባህር ዳር ከተማ
አለልኝ አዘነ ባህር ዳር ከተማ
ወንድማገኝ ኃይሉ ሀዋሳ ከተማ
አጥቂዎች
ቸርነት ጉግሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቢኒያም በላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ ሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገ/ሚካኤል ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኪቲካ ጀማ ኢት. መድን ድርጅት
ዱሬሳ ሹቢሳ ባህር ዳር ከተማ
ጌታነህ ከበደ ወልቂጤ ከተማ

ምንጭ 👉የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን