ከ120 ከሚበልጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር የቨርቹዋል ውይይት  ተካሄደ

በአለም አትሌቲክስ የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ቁጥራቸው ከ120 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር የቨርቹዋል ውይይት  ተካሄደ

እየተጠናቀቀ ያለውን የፈረንጆቹ 2022 ዓመትን ምክንያት በማድረግ በአለም አትሌቲክስ የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ቁጥራቸው ከ120 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር የቨርቹዋል ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ ላይ ፦

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፤

አቶ መኮንን ይደርሳል የብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ኃላፊ ፤

አቶ ሰለሞን አሰፋ የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ፕሬዝደንት ፤

ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ የኢትዮጵያ አሰልጣኞች ማህበር ፕሬዝደንት፤

የኢ.አ.ፌ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ከአለም አትሌቲክስ ጋር በመተባበር በፀረ-አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የቨርቱዋል ስብሰባ ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች የተንፀባረቁ ሲሆን አትሌቶች ስለመገኛ አድራሻና ስለ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ያላቸውን ግንዛቤ በመድረኩ አንፀባርቀዋል።

ምንጭ 👉 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.