ለ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ፈተና ተሰጠ

ለ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ፈተና ተሰጠ

በመጪው ታህሳስ 9 እና 10/2015 የሚጀመረው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ለሚመሩ የጨዋታ አመራሮች በዛሬው ዕለት የአካል ብቃት ፈተና ተሰጠ።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተከናወነው የአካል ብቃት ፈተና ላይ በድምሩ 125 የጨዋታ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በዋና ዳኛ ከተሳተፉት 61 ዳኞች መካከል 53 አልፈው 8 ዳኞች ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። በረዳት ዳኝነት ከተሳተፉት 64 ረዳት ዳኞች መካከል ደግሞ 60 ማለፍ ሲችሉ 4 ረዳት ዳኞች ሳያልፉ ቀርተዋል።
ረፋድ ላይ ከተከናወነው የአካል ብቃት ፈተና በማስከተል ከሰዓት በኋላ ለጨዋታ አመራሮች የጨዋታ ህጎች የክፍል ውስጥ ትምህርት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተሰጥቷል።

👉 ዘገባው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.