የእንግሊዝ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ለሴት ቡድን አሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።
የእንግሊዝ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ለሴት ቡድን አሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።
የእንግሊዝ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለሴት ቡድን አሰልጣኞች የሚሰጠው ስልጠና ተጀመረ።
የእንግሊዝ ኤምባሲ ”Great Football” በመባል ከሚታወቀው የሶፍት ፓወር ፕሮጀክት እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን ልጃገረዶች እግር ኳስ እንዲጫወቱና የሴት ቡድን አሰልጣኞች የእግር ኳስ አሰልጣኝነት ክህሎት ማብቃት ላይ ትኩረት በማድረግ ‘እግር ኳስ ለሰው ልጅ’ በሚል የአሰልጣኞች የማነቃቂያ ስልጠና ከዛሬ 05/04/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን በኦዌን ሳዝጌት እና የእግር ኳስ ለሰው ልጆች መስራች ቤሊ ቲዮንግኮ አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል።
ስልጠናው በቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ዛሬና ነገ በክፍል ውስጥ ከተሰጠ በኋላ የመዝጊያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተግባር በልጃገረዶች ፌስቲቫልና ውድድር ፕሮግራም ይጠናቀቃል።
በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በመገኘት ስልጠናውን ያስጀመሩ ሲሆን ለሰልጣኞች መልካም የሰልጠና ጊዜ በመመኘት ” ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጋር በዚህ አናበቃም። በመሰል ስልጠናዎች ላይ አብረን በጋራ በመሆን እንሰራለን።” ብለዋል።
ይህንን ስልጠና በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተመልምለው የመጡ 25 ያህል የሴት ቡድን አሰልጣኞች ስልጠናውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።
👉መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው