ቲቴ ከ ብራዚል አሰልጣኝነት ተሰናበቱ
ቲቴ ከ ብራዚል አሰልጣኝነት ተሰናበቱ
የብራዚል አሰልጣኝ ቲቴ በ2022 የፊፋ የአለም ዋንጫ ከክሮሺያ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ቡድናቸው ሳይታሰብ ከተሰናበተ በኋላ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
የ61 አመቱ ቲቴ ከጁን በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2016 ጀምሮ በብራዚል ቆይታው የነበራቸው ሲሆን 81 ጨዋታዎችን በአሰልጣኝነት በመምራት በሰባት ብቻ ሽንፈት አስተናግደዋል።
ሆኖም ዛሬ በተከናወነው የአለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በክሮሺያ ከተሸነፉ በኋላ ስራ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በቲቴ የእልጣኝነት ዘመን ብራዚል 61 ጨዋታዎችን አሸንፋ በ13ቱ አቻ ወጥታ በሰባት ብቻ ተሸንፋለች።