የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ 3ኛ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ 3ኛ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተካሄደዋል።
በምድብ ሀ 3 ሰዓት ላይ አዴት ከተማ በእውቀት አያልነህ ባስቆጠራት ግብ ሙከጡሪ ከተማን 1-0 ማሸነፍ ሲችል 5 ሰዓት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ ከአንጋጫ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2-0 አሸንፏል። የቢሾፍቱን ጎሎች ወንድማገኝ አብሬ እና የአንጋጫው ያቤፅ ዮሐንስ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል። 9 ላይ ሀዲያ ሌሞ ዳንግላ ከተማን 1-0 ሲያሸንፍ አስቻለው መኖር የድል ጎሉን ለሀዲያ ሌሞ አስቆጥሯል።
በምድብ ለ 3 ሰዓት ላይሻኪሶ ከተማ ማዕረግ መገርሳ ባስቆጠረው ጎል ወንዶ ገነትን 1-0 ሲያሸንፍ በመቀጠል የተካሄዱት የሞጆ ከተማ እና አማራ ውሃ ስራ ፣ የወሊሶ ከተማ ከ አምባ ጊዮርጊስ ጨዋታ በተመሳሳይ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
በምድብ ሐ 3 ሰዓት ላይ ልደታ ክፍለ ከተማ ሱሉልታ ከተማን 2-0 ሲያሸንፍ 5 ሰዓት ላይ ቡሬ ዳሞትን የገጠመው መቂ ከተማ 1-0 አሸንፏል። 9 ሰዓት ላይ ኑዌር ዞን ከ ጎፋ ባራንቼ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በኑዌር ዞን 2-1 አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በምድብ መ 3 ሰዓት ላይ በደሌ ከተማ ከሞጣ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በሞጣ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ዋሲሁን ሁሴን በደሌ ከተማን በ12ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ቢያደርግም አዳሙ ገለታ እና ብሩክ አያልነህ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ሞጣን አሸናፊ አድርገዋል። 5 ሰዓት ላይ ደባርቅ ከ ቡሌሆራ ተጫውተው 1-1 አቻ ሲለያኡ አማኑኤል አዳሙ ለደባርቅ ውብሸት ታዬ ለቡሌ ሆራ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታም መቱ ከተማ ከደጋን ከተማ በተመሳሳይ 1-1 ሲለያዩ ካሳሁን ግዛው ለመቱ ፣ ብርሃኑ ገብረየሱስ ለደጋን ከተማ አስቆጥረዋል።