የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አሳለፈ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 10ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 9ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አራት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 22 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አራት በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 29 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሶስት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች በሳምንቱ መርሃግብር ቡታቃ ሸመና(አርባምንጭ ከተማ)፣ ባዬ ገዛኸኝ (ሀዲያ ሆሳዕና) እና አምሳሉ ጥላሁን(ፋሲል ከነማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ሲወሰን እንዲሁም ባዬ ገዛኸኝ ከጨዋታ ሜዳ በተወገደበት ወቅት የዕለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት ከተቀጣው ቅጣት በተጨማሪ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000/ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦች ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ድሬዳዋ ከተማ ክለቡ ከ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛንና የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

እሁድ ህዳር 27/2015 ዓ.ም የሚካሄደው የሁለተኛ ሳምንት የወላይታ ድቻ እና የፋሲል ከነማ ተስተካካይ ጨዋታን በተመለከተ ጨዋታው ከ10 ወደ 12፡00 ሰዓት ተለውጧል። በተጨማሪነትም ፋሲል ከነማ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን 30ኛ ሳምንት በነበረ ቅጣት የሊጉ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያለ ደጋፊ እንደሚካሄድ የተላለፈው ውሳኔ በእንግዳ ቡድኑ(ፋሲል ከነማ) በኩል ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፇል።

በማለት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አወዳዳሪው አካል በድረገጹ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.