የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የመጀመርያ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ተካሂደዋል።
የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የመጀመርያ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ተካሂደዋል።
ምድብ ሀ
ሀዋሳ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ረፋድ 3 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ከ ቦሌ ክፍለ ከተማ 1-1 ተለያይተዋል። መብራቱ ተስፋዬ ለአአ ፖሊስ ፣ ፋግዶ ሽኩሪ ለቦሌ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ቀጥሎ በተደረገ ጨዋታ ሀዲያ ሌሞ በአስቻለው መኑር ጎሎች ዱከም ከተማን 2-0 ሲያሸንፍ ድሬዳዋ ፖሊስ ከ ዳንግላ ከተማ ያለ ግብ ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።
ምድብ ለ
አሰላ ላይ በሚደረገው የምድብ ለ ውድድር ወንዶ ገነት ቫርኔሮ ወረዳ 13ን ሙሀባ አደም እና ጌታቸው ቱሴ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2-0 ሲያሸንፍ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲና ዮሴፍ ጎል 1-0 አሸንፏል። በዕለቱ ሌላኛው መርሐ ግብርም ካራማራ አማራ ፖሊስን 2-1 አሸንፏል። መሐመድ አብዱልፈታ እና አብዱልመጂድ ሙሳ የካራማራን ፣ ሳሙኤል ይታያል የአማራ ፖሊስን ጎሎች አስቆጥረዋል።
ምድብ ሐ
ቢሾፍቱ ላይ እየተደረገ በሚገኘው የምድብ ሐ መርሐ ግብር አዲስ ቅዳም ከ አራዳ ክፍለከተማ 0-0 ሲለያዩ አረካ ከተማ ከ ጎፋ ባሬንቼ 1-1 ተለያይተዋል። ሶፎንያስ አየለ እና ሳምሶን ታሪኩ የየቡድኖቻቸውን ጎል በቅደም ተከተል አስቆጥረዋል። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐረር ከተማ ኑዌር ዞንን 4-2 ሲያሸንፍ ታረቀኝ ታደሰ፣ አቡሽ መንግስቱ፣ ካሌብ አበበ እና ስንሻው ዓለማየሁ የሐረርን ፣ ኮዌኬንግ ቦል እና አማኔ ቡአ የኑዌርን ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።
ምድብ መ
ደብረማርቆስ ላይ እየተከናወነ በሚገኘው የምድብ መ ውድድር ንፋስ ስልክ ላፍቶ በይልቃል እጅጉ እና ኤፌሶን ተስፋዬ (ራስ ላይ) ጎሎች ሾኔ ከተማን 2-0 ፣ መቱ ከተማ በአማኑኤል ንጋቱ ጎል ቤተል ድሪመርስን 1-0 አሸንፈዋል። ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ከ ደጋን ከተማ 1-1 ተለያይተዋል።
👉መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው።