ፖላንድ ከከፍተኛ ትንቅንቅ በኋላ ሳውዲ አረብያን አሸንፋለች
ፖላንድ ከከፍተኛ ትንቅንቅ በኋላ ሳውዲ አረብያን አሸንፋለች
ፖላዶች በዜሌንስኪ የ39ኛ ደቂቃ እና በሮበርት ሌዋንዶስኪ የ82’ኛ ደቂቃ ግቦች ታግዘው ነው ጨዋታውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል ።
በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት ሳውዲ አረብያዎች በ45’ኛው ደቂቃ ፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም አል ዳውሰሪ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።
በቀጣይ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሳውዲ አረቢያ ከ ሜክሲኮ እና አርጀንቲና ከ ፖላንድ የሚገናኙ ይሆናል።
በመጀመሪያው ጨዋታ ሳውዲ አረቢያ አርጀንቲናውያን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ ፖላንድና ሜክሲኮ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል ።
በምድቡ አርጀቲና ከ ሜክሲኮ ምሽት 4 ሰአት እስከሚጫወቱ
👉
ፖላንድ በ4 ነጥብና 2 ንጹህ ጎል አንደኛ
👉ሳውዲ አረብያ በ3 ነጥብና በ1 የግብ እዳ ሁለተኛ
👉ሜክሲኮን በ1 ነጥብ ያለምንም ግብ ሶስተኛ
👉አርጀንቲና ያለምንም ነጥብ በአንድ የግብ እዳ ደግም እግርጌ ላይ ተቀምጣለች ።