ኢራን ዌልስን አሸነፈች

ኢራን ዌልስን አሸነፈች

ህዳር 16 ቀን አርብ ቀን 7 ሰአት የምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታ ኢራን ዌልስን በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች አሸነፈች

👉ዌልስ 0-2 ኢራን
⚽️ ቼሳሚ 90+8′
⚽️ ሪዚአን 90+11′

ምሽት 4 ሰአት የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ጨዋታ እስከሚጠናቀቅ ኢራን እንግሊዝን ተከትላ ከምድቡ ሁለት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ትቀጥላለች።

በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢራን በእንግሊዝ 6 ለ 2 ስትሸነፍ ዌልስ ከአሜሪካ አንድ አቻ መለያየቷ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ኢራን የመጀመሪያውን 3 ነጥብ በማግኘት የማለፍ ተስፋዋን ስታሳምር ዌልስ ግን በመጀመሪያው ጨዋታ ከአሜሪካ ጋር አቻ ስትለያይ ባገኘችው አንድ ነጥብ ተወስና የማለፍ እድሏ የጠበበ ሆኗል።

ሁለቱ ቡድኖች የምድባቸውን የመጨረሻ ጨዋታ
ማክሰኞ ህዳር 20 ቀን 2015

ኢራን ከ አሜሪካ
ዌልስ ከ እንግሊዝ የሚጋጠሙ ይሆናል።

👇👇

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=567555512044496&id=100063701568018&mibextid=Nif5oz

Leave a Reply

Your email address will not be published.