ኢንግሊዝ ተጋጣሚዋን ረመረመች
ኢንግሊዝ ተጋጣሚዋን ረመረመች
በ2022ቱ የኳታር አለም ዋንጫ እንግሊዝ ተጋጣሚዋን ኢራንን በሰፊ የግብ ልዩነት በመርታት ምድቧን በበላይነት መምራት ጀምራለች ።
ኢንግሊዝ በቡካዮ ሳካ 2 ግቦች እንዲሁም በጃክ ግሪሊሽ ፣ በማርከስ ራሽፎርድ ፣ በጁድ ቤሊንግሀም እና በራሂም ስተርሊንግ ግቦች ታግዛ ነው ኢራንን 6 ለ 2 ያሸነፈችው ።
ኢራንን ከሽንፈት ያልታደጉ ሁለት ግቦች ደግሞ ታሬሚ አስቆጥሯል ።
በቀጣይ በምድቡ 2ኛ መርሀግብር ኢንግሊዝ አሜሪካን ስትገጥም እንዲሁም ኢራን ዌልስን ትገጥማለች ።