ህዳር 11 ቀን በድምቀት የሚከናው ታላቁ ሩጫን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

የፊታችን እሁድ ህዳር 11 ቀን በድምቀት የሚከናው ታላቁ ሩጫን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

ዛሬ ህዳር 9 ቀን ጠዋት በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት መድረክ ሰፋ ያለ ማብራሪያና መግለጫ ተሰጥቷል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ሰላማዊት ዳዊት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለዓለም እያስተዋወቀ የሚገኝ መድረክ ነው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ብለዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች የሆነው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ውድድሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአፍካንና የመላው ዓለም ቀልብ እየገዛ ይገኛል ብሏል።

ለ22ኛ ግዜ የሚከናወነውይህ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥመውታል፤ ቢሆንም ችግሮችን እየተቋቋመ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን ገልጿል።

ውድድሩ በቱሪዝም፣ በኢኮኖሚ፣ ሀገራችንን ከመጥቀሙ በተጨማሪ ተተኪ አትሌቶች በማፍራትና ሌሎች ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እያስገኘ እንደሚገኝና ይሄንን በበጎ መልኩ ማስቀጠል ይገባል በማለት አትሌቶችና ተሳታፊዎች በ10 ኪሎ ሜትሩ የጎዳና ላይ ሩጫ ላይ በጥሩ ስነ ምግባርና ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ውድድራቸውን እንዲያከናውኑ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ጥሪውን አቅርቧል።

ከነገ በስትያ ህዳር 11 ቀን መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚከናወነው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ 40 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ

በዋናው የፉክክር ውድድር ላይ በሁለቱም ጾታዎች በአጠቃላይ 500 አትሌቶች ይወዳደራሉ።

በኢትዮጰያ በኩል በሴቶች 👉 ፎተን ተስፋይ ፣ዘይነባ ይመር፣ እና ደራ ዲዳ ሌሎች
በወንዶች 👉ገመቹ ዲዳ ፣ሞገስ ጥዑማይ፣ እና አማረ እና ሌሎች ይሳተፉሉ ።

ከተጋባዥ ሀገራት በወንዶች👉 ኬንያውያኑ ቪክቶር ሙቲና ቪክቶር ኪፕሩቶ እንዲሁም
👉ዩጋንዳውያኑ አላን ኪቤት ኬኔት ኪፕሮፕና ይሮጣሉ።
👉በተጨማሪም ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና የኬንያ የቀድሞ የረጅም ርቀት ሯጭ ሞሰስ ታኑይ በውድድሩ ላይ በክብር እንግድነት ይታደማሉ።

በወንዶችና በሴቶች ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች በቅደም ተከተል 150 ሺህ፣ 50 ሺህ እና 30 ሺህ ብር ሽልማት ይሰጣቸዋል።
ለውድድሩ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ 255 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ተነግሯል ።

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች የሆነው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ለተጋባዥ የክብር እንግዶች የኢትዮጵያን ባህል የሚያንፀባርቅ በልዩ ሁኔታ የተሰራ ጋቢ በሽልማት አበርክቷል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.