በቱርክ ኢስታቡል በተካሄደ የ2022 የኢስታቡል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ሴት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመግባት ውድድሩን  አሸንፈዋል።

እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2015 በቱርክ ኢስታቡል በተካሄደ የ2022 የኢስታቡል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ሴት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመግባት ውድድሩን  አሸንፈዋል።

👉ሴቻሌ ዳላሳ 2:25:53 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች።

👉መለሰች ፀጋየ 2:28:59 በሆነ ሰዓት በመግባት 2ኛ በመሆን አጠናቃለች።

👉እታለማሁ ስንታየሁ 2:31:35 ሰዓት በማስመዝገብ 3ኛ ሆና ጨርሳለች።

👉በወንዶች ኬንያዊዉ ሮበርት ኪፕ ኬምቦይ 2:10:16 በሆነ ሰዓት በመጨረስ 1ኛ ሆኗል።

👉የባህሬኑ አትሌት ማሪዉስ ኪሙታይ 2:10:25 በማስመዝገብ 2ኛ ሲወጣ።

👉ሌላኛዉ ኬንያዊ ሲላ ኪፕቶ 2:11:40 በመግባት 3ኛ ሆኗል።

ኢትዮጵያዊዉ ታደሰ 2:11:57 በመግባት አምስተኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.