ሲቲዎች ጣፉጩን 3 ነጥብ አሳክተዋል
ማንችስተር ሲቲዎች በኤርሊንግ ሀላንድ የመጨረሻ ደቂቃ ጎል ታግዘው ፉልሃም 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።
ጁሊያን አልቫሬዝ በ16’ኛው እና ኤርሊንግ ሀላንድ 90+4ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ አንድሬ ፔሬራ ፉልሃምን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ በ28′ ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል ።
ማንችስተር ሲቲዎች ነጥባቸውን ሰላሳ ሁለት በማድረስ የሊጉን መሪነት ከአርሰናል በጊዜያዊነት ሲረከቡ ፉልሀም በአስራ ዘጠኝ ነጥቦች ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሌሎች የሊጉ መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ እና ብራይተን ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል።
በቀጣይ ማንችስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ እንዲሁም ፉልሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
ሌሎች በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች
ሊድስ ዩናይትድ 4-3 በርንማውዝ
⚽️ ሮድሪጎ 3’Pk ⚽️ ታቨኒየር 7′
⚽️ ገሪንውድ 60′ ⚽️ ቢሊንግ 19
⚽️ ኮፐር 68′ ⚽️ ሶላንኬ 49′
⚽️ ሲመርሺል 84′
ኖቲንግሀም 2-2 ብሬንትፎርድ
⚽️ ጊብስ ኃይት 20′ ⚽️ ምቤሞ 45′
⚽️ ጊብስ ኃይት 90+’ ⚽️ ዊሳ 75′
ወልቭስ 2-3 ብራይተን
⚽️ ጌዴሽ 13′ ⚽️ ላላና 10′
⚽️ ኔቬስ 34’Pk ⚽️ ሚቶማ 44′
⚽️ ግሮስ 84′