ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት በተካሄደዉ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸነፈ።
የድሬዳዋ ከተማን 3 የማሸነፊያ ጎሎች አሳንቴ ጎድፍሬድ በ49ኛዉ ቢኒያም ጌታቸዉ በ60ኛዉ ዮሴፍ ዮሀንስ በ65ኛዉ(ፍ) ደቂቃ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ አንተነህ ተፈራ በ93ኛዉ ደቂቃ አስቆጥሯል።
በቀጣዩ 7ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከመቻል ሀሙስ ህዳር 1 ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ የሚጫወት ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ እሁድ ህዳር 4 10:00 ሰዓት ላይ ይጫወታል።