የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታንዛንያ ጋር 2 አቻ ተለያየ

በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ዛሬ ምሽት በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታንዛንያ ጋር 2 አቻ ተለያየ።

ለኢትዮጵያ ቡሄራዊ ቡድን ዮሴፍ ታረቀኝ በ31ኛዉ ከድር አሊ በ87ኛዉ ደቂቃ ጎሎችን አስቆጥረዋል።

የታንዛኒያን የአቻነት ጎል ዲክሰን ቫላንቲኖ በ21ኛዉ ደቂቃ አቱማኒ ማካንቦ በ49ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.