የአዉሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የማክሰኞ ምሽት መርሃግብር ጨዋታዎች ውጤት
ትናንት በአዉሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ መርሃግብር በተካሄደ ጨዋታ ሊቨርፑል ናፖሊን 2 ለ 1 አሸነፈ።
የሊቨርፑልን 2 ጎሎች ሳላህ በ 86 እንዲሁም ኑኔዝ በጭማሪ ሰዓት በ98ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።
ባርሴሎና ቪክቶሪያ ፕሌዘንን 4 ለ 2 ሲያሸንፍ አሎንሶ በ6ኛዉ ቶሬስ በ44ና በ54ኛዉ እንዲሁም ቶሬ በ75ኛዉ ደቂቃ የባርሴሎናን 4 የማሸኘፊያ ጎሎች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸዉ።
የቪክቶሪያ ፕሌዘንን 2 ጎሎች ቾሪ በ51ኛዉና በ63ኛዉ ደቂቃ አስቆጥሯል።
ባየር ሙኒክ ኢንተርሚላንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ጎሎቹን ፓቫርድ በ32 ሞቲንግ በ72ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።
በሌላ የአዉሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቶተንሀም ማርሴይን 2 ለ 1 አያክስ ሬንጀርስን 3 ለ 1 ፍራንክፈርት ስፖርቲንግ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ቀደም ብሎ 2:45 በተደረጉ ጨዋታዎች ፖርቶ አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል። ታሬሚ በ6ኛዉ ደቂቃ ኢዩስታኩዮ በ24ኛዉ ደቂቃ የፖርቶን የማሸነፊያ ጎሎች ሲያስቆጥሩ ኢቫን ማርካኖ የአትሌቲኮ ማድሪድን ብቸኛ ጎል በጨዋታ መጠናቀቂያ 96ኛዉ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ሌቨርኩሰን ከ ክለብ ብሩጅ 0 ለ 0 በሆነ ዉጤት ተለያይተዋል።