ኬኒያውያን በነገሱበት የፍራንክፈርት ማራቶን አትሌት ዴሬሳ ገለታ 3ኛ በመሆን ዉድድሩን አጠናቋል።

በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዴሬሳ ገለታ 2:07:30 ሰዓት በማስመዝገብ 3ኛ በመሆን ዉድድሩን አጠናቋል።

ኬንያዊዉ ብሪሚን ኪፕኮሪር 2:06:11 በሆነ ሰዓት በመግባት 1ኛ ሲሆን ኬንያዊዉ ሳምዌል ንያማይ 2:07:19 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሁኖ አጠናቋል።

ሌላኛዉ ኢትዮጵያዊ ባለዉ ይሁኔ 2:09:21 በሆነ ሰዓት በመግባት 4ኛ ሆኖ አጠናቋል።

በሴቶች የማራቶን ዉድድር ኬንያዊቷ ሰሊ ችፕየጎ 2:23:11 ሰዓት በማስመዝገብ 1ኛ ሁና አጠናቃለች። ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃዎች የተያዙትም በኬንያዉያን አትሌቶች ነዉ።

ኢትዮጵያዊቷ መሰረት አበባየሁ 2:29:21 በሆነ ሰዓት በመጨረስ 7ኛ ሆና ዉድድሩን አጠናቃለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published.