የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ-ሥርዓት የሚከናወንበት ዕለት ተቀየረ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ-ሥርዓት የሚከናወንበት ዕለት ላይ ለውጥ ተደርጓል።

የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ከዚህ ቀደም ጥቅምት 22/2015 እንደሚከናወን ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ለውጥ ማድረግ በማስፈለጉ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 በጁፒተር ሆቴል የሚከናወን ይሆናል።

የምዝገባ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሠረት ጥቅምት 25 እንዲሁም የውድድር መጀመርያ ጊዜ ህዳር 10 የሚከናወን መሆኑን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.