የከፍተኛ ሊግ የተሳታፊ ቁጥርን በሒደት ለመቀነስ ውሳኔ ተላለፈ!

የከፍተኛ ሊግ የተሳታፊ ቁጥርን በሒደት ለመቀነስ ውሳኔ ተላለፈ!

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ኮሚቴ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር በየዓመቱ በሒደት በመቀነስ ሊጉን ለማስተዳደር አመቺ በሆነ እና ወደ ገበያ እድልነት በሚቀይር መልኩ ጥራቱን ከፍ ለማድረግ ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት የ2015 የውድድር ዓመት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር መሳተፍ ያልቻሉ ክለቦችን ጨምሮ 42 ክለቦች በሦስት ምድቦች ተወዳዳሪ የሚሆኑ ሲሆን በየምድቡ 14 ክለቦች ተሳታፊ በማድረግ በዓመቱ መጨረሻ ከየምድቡ የመጨረሻ 5 ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ በአጠቃላይ 15 ክለቦች ወደ አንደኛ ሊግ እንዲወርዱ ተደርጎ ከአንደኛ ሊግ ደግሞ ለ2016 የውድድር ዘመን 4 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድጉ ተወስኗል።

ይህም በ2016 የሚሳተፉ ክለቦችን ቁጥር በመቀነስ ሦስት የነበረውን ምድብ ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከFIFA ጋር በመነጋገር በፊፋ ፕላስ ፕሮጀክት በኩል ውድድሩ የቀጥታ የኦንላይን ስርጭት እንዲያገኝ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ይህም የውድድሩን ደረጃ ከፍ ለማድረግ አይነተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥራትን ከፍ ለማድረግ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ ስራዎች እንደሚሰሩ ዛሬ በአፍሮዳይት ሆቴል ከሊጉ ክለቦች ጋር በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.