የከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ጊዜ ላይ ሽግሽግ ተደረገ

የከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ጊዜ ላይ ሽግሽግ ተደረገ

በዛሬው እለት በአፍሮዳይት ሆቴል የ2015 የውድድር ዘመንን ከሌላው ጊዜ የተሻለ ለማድረግ በሚያስችሉ ሀሳቦች ዙርያ ከውድድሩ መጀመር አስቀድሞ ከተሳታፊ ክለቦች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

የውድድሩ ጊዜ ህዳር 3 እንዲጀመር መወሰኑ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የዝግጅት ጊዜ እንደሚያጥራቸው በመግለፅ እንዲራዘም ከተሳታፊ ክለቦች የተነሳውን ጥያቄ ከግምት በማስገባት የውድድሩ መጀመርያ ጊዜ ላይ ሽግሽግ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ክለቦች እስከ ህዳር 9 ድረስ የሚጠበቅባቸውን የዳኞች እና ታዛቢዎች እንዲሁም የምዝገባ ክፍያ በማጠናቀቅ ምዝገባ ፣ ህዳር 10 የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርአት እንዲሁም ውድድሩ ህዳር 17 እንዲሆን ተወስኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.