አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በአሜሪካ ተሸለመ

በአሜሪካ ቨርጂኒያ በኢትዮጵያዉያን በተዘጋጀዉ Impact Award ላይ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ተሸላሚ ሆኗል።

በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የኒዉካርልተን ከተማ ከንቲባ የተገኙ ሲሆን October 16 በከተማዋ የቀነኒሳ ቀን ተብሎ እንዲሰየም መወሰናቸዉን አብስረዋል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሽልማቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለና ከኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እጅ ተቀብሏል።

በፕሮግራሙ የአትሌቱ ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ለቤተሰቡና ለሽልማቱ አዘጋጆች ምስጋና አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.