አላንታ ላዚዮን አሸነፈ

በ11ኛ ሳምንት የጣልያን ሴሪዬ አ መርሀ ግብር በስታድዮ አትሌቲ አዙሪ ዲታልያ በአላንታ እና በላዚዮ መካከል በተደረገ ጨዋታ ላዚዮ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለላዚዮ የማሸነፊያ ግቦቹን ማቲያ ዛካኚ እና ፌሊፔ አንደርሰን አስቆጥረዋል።

የአትላንታዉ ሉዊስ ሙሪዬል በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ላዚዮዎች በ24 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

አላንታዎች በተመሳሳይ 24 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጠው አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ የሴሪዬ አ ጨዋታ ላዚዮዎች የዛሬ ሳምንት ሳሌርኒታናን በሜዳቸው ይገጥማሉ።በአንፃሩ አታላንታዎች ወደ ኤምፖሊ ተጉዘው ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ቶሪኖ ዩዲኒዜን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ አይና በ14ኛዉ ፔሌግሪ በ69ኛዉ ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎችን አስቆጥረዋል። ዲዮሎፊ የዩዲኒዜን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።

ዩዲኒዜ በ21 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቶሪኖ በ14 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቦሎኛ ሊቼን 2 ለ 0 በሆነ ዉጤት መርታት ችሏል። የቦሎኛን የማሸነፊያ ጎሎች አርኖቶቪች በ13ኛዉ ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም ፈርጉሰን በ34ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።

ቦሎኛ በ10 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሊቼ በ8 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.