ሲዳማ ቡናና አርባ ምንጭ ከተማ ተቀጡ

በሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በተከሰቱ ጥፋቶች ላይ ሊግ ካምፓኒው ቅጣት ጣለ።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2015 የውድድር ሦስተኛ ሳምንት ላይ የሊግ ካምፓኒው የውድድር እና ሥነ ስርዓት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የደረሱትን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ በሁለት ክለቦች ላይ ቅጣት አስተላልፏል፡፡
ሲዳማ ቡና በቅዱስ ጊዮርጊስ በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱ ዳኛ ላይ አፀያፊ ስድብን በመሰንዘራቸው የ50 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል።
አርባምንጭ ከተማ መቻልን ባሸነፈበት ጨዋታ የአርባምንጩ በረኛ አቤል ማሞ የተመዘገበ የመለያ ቁጥሩ 1 ሲሆን 99 ለብሶ ወደሜዳ መግባቱን ተከትሎ ቁጥር በመቀየሩ በተጨማሪም ሊግ ካምፓኒው ከ1 እስከ 50 ቁጥር ብቻ ተጫዋቾች መጠቀም አለባቸው የሚለውን ህጉን ስለጣሰ በሁለቱ ጥፋቶች ክየ6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.