ኢትዮጵያ ታላቁን የስፖርት ሰው አጣች

የስፖርት ጋዜጠኛች የማህበር መስራችና፣ በካፍ እና ፊፋ ውስጥ ለረጅም አመታት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲታገሉ የነበሩትና በስፖርት ጋዜጠኝነት እና በአመራርነት የሚታወቁት አንጋፋው የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ባለፈ እስከ ካፍ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራርነት ድረስ ግልጋሎት የሠጡ አንጋፋ የስፖርት ሰው ነበሩ ።

ከአቶ ፍቅሩ ስራዎች መካከል

👉 የፒያሳ ልጅ የሚል መጸሀፍ በማሳተም  እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን ስራ እያዋዙ በማቅረብ ተወዳጅነትን አትርፈዋል።

👉 የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላለፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ናቸው ።

👉 ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የስፖርት ዘገባዎችን አቅርበዋል

👉 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  በካፍ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ በአመራርነት ሰርተዋል

ኢትዮጵያን ስፖርት በአቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ህልፈት ሀዘኑን ይገልጻል
ለመላው ስፖርት አፍቃሪያን እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.