በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለደጋፊዎች የወጣው ሕግ
ሊጀመር ከ50 ቀናት በታች የቀሩት
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለደጋፊዎች የወጣው ሕግ !
የ2022ቱን የዓለም ዋንጫ የምታስተናግደው ኳታር የዓለም ዋንጫውን በስቴዲየሞች ተገኝተው በሚታደሙ ደጋፊዎች ላይ ጠንከር ያለ ሕግን አውጥታለች ፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የሆነችው ኳታር በ2022 ለምታስተናግደው የአለም ዋንጫ ውድድር የኳታር እግር ኳስ ፌደሬሽን ከዚህ በፊት ተተግብረው የማይታወቁ እና ከእስር እስከሞት ድረስ የሚያስቀጡ ሕጎችን እና ደንቦችን በተለየ መልኩ በደጋፊዎች ላይ ማውጣቱን ተከትሎ እሰከ አሁን ከተዘጋጁ የአለም ዋንጫ ውድድሮች በህግ ና በደንብ የታጠረ የአለም ዋንጫ ሊያደርገው ይችላል።
የአለም ዋንጫውን ለመከታተል ወደሀገሪቱ የሚገባ ማንኛውም ደጋፊ ጨዋታዎች በሚደረጉበት ቦታ እና ሰዓት የአልኮል መጠጥ መግዛትም ይሁን መጠጣትን አይፈቀድለትም፡፡
አልኮልን መጠጣት የሚፈልግ ደጋፊ በተከለለ ስፍራ እና በተወሰነ የሰዓት ገደብ ውስጥ ሆኖ መጠቀም እንደሚችልም ሕጉ ይደነግጋል፡፡ይህንን ሕግ ተላልፎ የተገኘ እንዲሁም አደንዛዥ እጾችን ሲጠቀም የተገኘ ተመልካች ወይም ደጋፊ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል፡፡
ከተቃራኒ ጾታ ጋር በአደባባይ ወይም በግልጽ መሳሳም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን በተለይ ደግሞ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ያላቸውን እስከሞት በሚደርስ ቅጣት እንደሚቀጣ ይደነግጋል።
ከአለባበስ ጋር በተያያዘ በተለይ ሴቶች ትከሻቸውን የሚያሳይ እና አጫጭር ቀሚሶችን መልበስ የተከለከለ ሲሆን ይህንን ሕግ ተላልፎ የተገኘ ሰው በእስር ሊቀጣ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
የ2022ቱን የአለም ዋንጫ ውድድር ለሚታደሙ ተመልካቾች እንደልባቸው እንዳይዝናኑ እና በጥንቃቄ ውስጥ ሆነው መዝናናትን እንዲመርጡ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይጠበቃል ።