የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ዛሬ ጅማሮውን ያገኛል

ተወዳጁ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ዛሬ በእለተ ማክሰኞ ጅማሮውን ሲያገኝ ከምሽቱ 3:30 ላይ የአሰልጣኝ ፓትሪክ ቪዬራው ክርስቲያል ፓላስ በሰለርስት ፓርክ ስታዲየም ብሬንትሮርድን ያስተናግዳል ።

በክርስቲያል ፓላስ በኩል የዊልፍሬድ ዛሀ የመሰለፍ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል ሲሉ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ገልፀዋል ።

👉 ፉልሀም ከ ብራይተን

በተመሳሳይ ሰዓት አዲስ አዳጊው ፉልሃም ከአርሰናኑ ሽንፈት ለማገገም በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ጠንካራውን ብራይተንን ይገጥማል ። ብራይተኖች በበኩላቸው 3 ድሎች እና 1 የአቻ ውጤትን አስመዝግበው በኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ደረጃ ሠንጠረዥ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

👉 ሳውዝአምተን ከ ቼልሲ

3:45 ሲል ደግሞ በሴንት ሜሪ ስታዲየም ሶውዝአምፕተኖች የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲን ያስተናግዳሉ ።

ከቀናት በፊት በሴንት ሜሪ ስታዲየም በማንቸስተር ዩናይትድ የ1 ለ 0 ሽንፈት የደረሰባቸው የራፍ ሀትልሰኑ ክለብ ሳውዝአምፕተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የቶማስ ቱሄሉን ክለብ ይገጥማሉ ።

ቼልሲዎች በበኩላቸው በስታንፎርድ ብሪጅ ሌስተር ሲቲን በ10 ተጫዋች 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈው ነው ሳ.አምፕተንን የሚገጥሙት ።

በቼልሲ በኩል ንጎሎ ካንቴ በጉዳት እና ኮኖ ጋላገር በቅጣት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው ። ሴኔጋላዊው ተከላካይ ካሊዶ ኩሊባሊም ቅጣቱን ጨርሶ ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ተናግረዋል ።

👉 ሊድስ ከ ኤቨርተን

ምሽት 4:00 ላይ ሊድስ ዩናይትድ የፍራንክ ላምፓርዱን ኤቨርተንን ያስተናግዳል ።

የአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርዱ ኤቨርተን የውድድር አመቱ ከጀመረ አንስቶ በፕሪሚየር ሊጉ ምንም አይነት አለማሸነፋቸው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርን ጫና ውስጥ ቢከታቸውም በዚህ ጨዋታ ለሊድስ ቀላል ተጋጣሚ አይሆኑም ።

ሊድሶችም በበኩላቸው ከብራይተን የ 1 ለ 0 ሽንፈት በኋላ በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማሉ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.