አስደማሚ ድል ስድስተኛው ወርቅ ገቢ ሆኗል ኢትዮጵያ ከአለም 3ኛ ሆነች
በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የ3000ሜ. መሠ. ወንዶች የፍፃሜ ወድድር ኢትዮጵያዊውን ሳሙኤል ዱጉና በ8.37.92 በመግባት በአንደኛነት በማጠናቀቁ ለለገሩ ኢትዮጵያ ስድስተኛውን ወርቅ አስገኝቷል ።
ሌላው ኢትዮጵያዊ ሳሙኤል ፍሬው በ8.39.11
በመግባት ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ ገቢ አድርጓል ።
በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች አትሌቶቻችን ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል ።
የአለም ወጣቶች ሻንፒዮን ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያዉያን በመጨረሻው ቀን ባሸነፋባቸው አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች በመታገዝ በጠቅላላው በ6 ወርቅ በ5ብርና በ1 ነሀስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል ።
ውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቀችው ጃማይካ በ6 ወርቅ በ7 ብርና በ3 ነሀስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች ።
ውድድሩን በአንደኛነት ያጠናቀቀችው አሜሪካ በ7 ወርቅ በ4 ብርና በ4 ነሀስ በድምሩ 15 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም አንደኛ በመሆን አጠናቃለች ።
አፍሪካዊቷ ጎረቤታችን ኬኒያ በ3 ወርቅ በ3 ብርና በ4 ነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም አራተኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች ።