የ2022/23 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ጅማሮውን ያገኛል ።

አንጋፋው እና ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በለንደን ደርቢ ሰለርስት ፓርክ ስታዲየም ላይ ጅማሮውን ያገኛል ።

በ2022/23 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ሁለቱን የቀድሞ የአርሰናል አንበሎች አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታን እና አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራን ያፋጥጣል ።

ባሳለፍነው አመት የሻምፒዮንስ ሊጉን ቦታ ለማግኘት ከጫፍ ደርሰው የነበሩት አርሰናሎች በአሠልጣኝ ፓትሪክ ቬራ የሚመሩትን ክርስቲያል ፓላስን ይገጥማሉ ።

የሰሜን ለንደኖቹ አርሰናሎች በአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ እየተመሩ የውድድር አመቱን ሲጀመሩ የደቡብ ለንደኖቹ ክርስቲያል ፓላሶችም በበኩላቸው በአጥቂያቸው ዊልፍሬድ ዛሃ ታግዘው የ2022/23 የውድድር ዓመት ይጀምራሉ ።

ባሳለፍነው የውድድር አመት በሰለርስት ፓርክ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ክርስቲያል ፓላስ አርሰናልን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል ። በኤመሬትስ ስታዲየም ላይ ባደረጉት ጨዋታ ደግሞ ሁለት እኩል በሆነ ውጤት ተለያይተዋል ።

ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጀመራል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.