አትሌቲክስ ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ሽልማትም ተበረከተላቸው

በ18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን
በእስጢፋኖስ ፣ 4 ኪሎ ፣ ፒያሳ ፣ ቸርችል አደባባይ ፣ሰንጋተራ ፣ሜክሲኮን በመዞር በለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ በግልጽ መኪና ደስታቸውን ከህዝቡ ጋር አሳልፈዋል።
በቤተመንግስትም ከፍተኛ ባለስልጣናት ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በክብርት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኩል የተለያዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ከተሳታፊ አትሌቶች ጀምሮ ለሁሉም እንደየድርሻቸው ተሸልመዋል። ለጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሎ 40 ኪሎግራም ወርቅ በልዩ ዲዛይን እንደሚሠራላት ተነግሯል በቀጣይ ከክልል መስተዳደሮች እና ከተሞች ተጨማሪ ሽልማቶች እና የመሬት ስጦታ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

👉ዝርዝር ሽልማቱን ከታች ይመልከቱ
👉ሀሳብ ፣አስተያየት ፣ጥቆማ፣ቅሬታ ካለ ሀሳብዎን ይስጡ
በፈቃደኝነት ላይክ ኮሜንት ሼር ያድርጉ እናመሰግናለን ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.