ኢትዮጵያዉያን ጀግኖች ማጣሪያውን አልፈዋል
አሁን በተጠናቀቀ በኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5000 ሜትር የመጀመሪያ ማጣርያ የተካፈሉት ሁለት ኢትዮጵያዉያን ጉዳፍ ፀጋዬ በ14.52.64 በአንደኛነት እንዲሁም ዳዊት ስዩም 14.53.06 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜው ውድድር አልፈዋል ኪኒያውያን ቺቤት እና ክሊሞ ሶስተኛ እና አራተኛ በመሆን ተያይዘው ገብተዋል። በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ ለተሰንበት ግደይ እየተወዳደረች ትገኛለች ።