አትሌት ለተሰንበት ግዳይ ዛሬ በኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ላይ ስትሳተፍ ሌሎች መርሀ ግብሮችም ይደረጋሉ

በኦሪገን የሚካሄደው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም በእለተ ቅዳሜ ሲቀጥል
ምሽት 2:35 ላይ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ሲምቦ አለማየሁ ፣ መቅደስ አበበ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ።
ምሽት 4:20 ላይ ተጠባቂው የሴቶች 10 ሺ ሜትር ፍፃሜ የሚደረግ ሲሆን ለተሰንበት ግዳይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ቦሰና ሙላቱ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ሲሆኑ ውድድሩም ከወዲሁ ቀልብ ስቧል ።
የኦሪገን 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሊትም ሲቀጥል 10:30 ላይ የወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ይደረጋል ሳሙኤል ተፈራ ፣ ሳሙኤል አባተ እና ታደሰ ለሚ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ።
ለሊት 11:05 ላይ ደግሞ የሴቶች የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ሲደረግ ጉዳፍ ፀጋየ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.