በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል

በኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ኢትዮጵያዊያኖቹ ወርቅ ውሃ ጌታቸው እና መቅደስ አበበ ወደ ፍፃሜው መግባታቸውን አረጋግጠዋል ።

ሴምቦ አለማየሁ 5ኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለችም ።

ውድድሩ በሶስት ዙር ሲደረግ ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተናጥል (ለየብቻ) ነበር ውድድራቸውን ያደረጉት ። በመጀመሪያ በተደረገው ውድድር ኢትዮጵያን የወከለችው ውሃወርቅ ጌታቸው ትውልደ ኬንያዊ ግን በዜግነት ካጃኪስቲያናዊዋ ጃሩቶ በሰፊ እርቀት አስፍታ መርታ አንደኛ ብትወጣም ወርቅውሃ በሁለተኝነት ወጥታ በቀጥታ ወደ ፍፃሜው አልፋለች ።

በቀጣይ በተደረገው ሌላው የሴቶች 3000 ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ አበበ በውድድሩ በኡጋንዳዊዋ ቸሙታይ ከባድ ትንቅንቅ ቢገጥማትም በውድድሩ መጨረሻ ላይ ፈረንሳዊቷ አሊስ ፊኖት ተምዘግዝጋ ወጥታ አንደኛ በመሆን ስትጨርስ ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ አበበ በድንገት የመጣችውን ፈረንሳዊቷን መቅደም ባትችልም በሁለተኝነት በማጠናቀቅ ወደ ፍፃሜው ማለፏን አረጋግጣለች ።

መቅደስ አበባ በ3000 ሜትር መሰናክል አስገራሚ እና ተስፋ ሰጪ ብቃቷን ስታሳይ በእጅጉ ተጠብቃ ውድድሩንም እስከ መጨረሻ ድረስ ስትመራ የነበረችው ኡጋንዳዊቷ ቸሙታው 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።

በመቀጠል 3ኛው እና የመጨረሻው ዙር የ3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያን የወከለችው ሲምቦ አለማየው አሪፍ አጀማመር ብታደርግም በመጨረሻም 5ኛ ሆና ማጠናቀቋ ወደ ፍፃሜው ሳታልፍ ቀርታለች ።

 

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በፍፃሜው በወርቅውሃ ጌታቸው እና በመቅደስ አበበ ስትወከል ፍፃሜውም ረዕቡ ሐምሌ 13 ከለሊቱ 11:45 የሚደረግ ይሆናል ።

One thought on “በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.