በሮም ከተማ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር
▪️በጣልያኗ ከተማ ሮም በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈውበታል።
▪️በ1,500ሜትር በተካሄደ ውድድር
ሂሩት መሸሻ 4:03:79 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሯን ስታጠናቅ
አክሱማዊት እምባዬ 4:04:53 በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
▪️በ3000 ሜትር መሰናክል በተካሄደ ውድድር
የምንግዜም 12ኛ ፈጣን ሰአት አስመዝጋቢው እንዲሁም የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ በአስደናቂ አጨራረስ 7:59:23 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሩን ሲያጠናቅ ኬንያዊው አብርሀም ኪብዮት 8:06:73 ከሱ 1 ማይክሮ ሰከንድ በመዘግየት ሌላው ኢትዮጵያዊ ጌትነት ዋሌ 8:06:74 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
▪️ተጠባቂ በነበረው የ5000 ሜትር ወንዶች ውድድር።
ኪሜሊ ኪፖሪ በ2014 በኤሊውድ ኪፕቾጌ ተይዞ የነበረውን እና የቦታውን እንዲሁም የግሉን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ 12:46:33 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሩን ሲያጠናቅ ሌላው ኬንያዊ ጄኮፕ ክሮፕ12:46:79 ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጀልቻ 12:52:10 ሶስተኛ ደረጃን ሲይዙ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሰለሞን ባረጋ 12:54:84 በመግባት 4ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ሚካኤል ደጀኔ ።