ስደተኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ፈርኦኖቹ ላይ አመርቂ ድል ተጎንፆፏል።

▪️በኮትዲቫር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን ከግብፆ አቻው ጋር ያካሄዱት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2-0 በሆነ ውጤት ረተዋል።

▪️ካፍ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟላ ስቴዲየም ኢትዮጵያ ውስጥ ባለመኖሩ የትኛውም የኢንተርናሽናል ጨዋታዎች በሜዳችን እንዳናርግ መከልከላችን የሚታወስ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለሜዳ ኪራይ ወደ ጎረቤት ብሎም ራቅ ወዳሉ አፍሪካ ሀገራት ስደት መውጣቱ የሚታወስ ነው። ታዲያ ጎረቤት ሀገር ግብፅ ምንም ወጪ ሳታወጡ በሜዳችን ጨዋታችሁን አድርጉ የሚል ሀሳብ ብታነሳም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው የ90 ደቂቃ ብቻ ሳይሆን የክብርም ጭምር መሆኑን በመግለፆ ሳይቀበለው ቀርቷል። የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ ባካሄደበት የማላዊው ቢንጉ ስቴዲየምን በመከራየት የግብፆ አቻውን አስተናግዶ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ጭምር ማሸነፍ ችሏል።

▪️ኢትዮጵያ 2 – 0 ግብፅ
⚽️ ዳዋ ዩቴሳ
⚽️ ሽመልስ በቀለ

▪️የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር እንዲሁም ኢላማቸውን በጠበቁ ሙከራዎች ታጅበው ወሳኙን 3 ነጥብ ማሳካት ችለዋል።

▪️ የግብፆ ብሄራዊ ቡድን 2 ግቦችን ብቻ ማስተናገዱ እድለኛ በሚያደርገው መልኩ ብሄራዊ ቡድናችን እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴ ማድረግ ችለዋል።

▪️እዚህ ምድብ ላይ የሚገኙት ጊኒ እና ማላዊ ጨዋታቸውን አድርገው መደበኛው ሰአት ተጠናቆ በተጨመሩት ደቂቃዎች ላይ ጊኒ ግብ በማስቆጠር 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

▪️ብሄራዊ ቡድናችን የመጀመሪያ 3 ነጥቡን በማሳካት በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ መቀመጡን አረጋግጧል። በ3 ነጥብ እንዲሁም በ 1 ንፁህ ግብ 1ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ማላዊ እና ጊኒ በእኩል 3 ነጥብ ምንም ንፁህ የግብ ክፍያ ባለመያዝ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ግብፆ በእኩል 3 ነጥብ 1 የግብ እዳ በመያዝ የምድቡ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገዳለች።

#እንኳን_ደስ_አለን። 🇪🇹

ሚካኤል ደጀኔ ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.