በ ኦስትራቫ ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታ አስደናቂ ድል ተጎናጸፋ።

በ ኦስትራቫ ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታ አስደናቂ ድል ተጎናጸፋ።

2022 ኦስትራቫ የእሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታ ደምቀው አምሽተዋል።

300ዐ ሜ መሰናክል ወንዶች ለሜቻ ግርማ በራሱ ተይዞ የነበረን የሀገራችንንና የግሉን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፏል።

ለሜቻ በ2019 በዶሀ ያስመዘገበውን የግል 8:01.36 ሰዓትን በኦስትራቫ 7:58: 68 በመሮጥ አሻሽሎታል።


ሌላኛው ተወዳዳሪ ሀይለማሪያም ተገኝ ከለሜቻ ፤ ከጌትነት፤ ከሮባ ጋሪ እና ከጫላ ባዮ በመቀጠል የሀገራችን 5ኛው ፈጣን ሰዓት(8:07:70) በማስመዝገብ ጭምር ሁለተኛ ለመውጣት ችሉዋል።
በተጨማሪም አብርሀም ስሜና ሳሙኤል ፍሬው አራተኛና አምስተኛ ሆነው ጨርሰዋል።

በ 800ሜትር በወንዶች በተከናወነ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ቶሎሳ ቦደና በኬንያዊው አትሌት ኮሊስ ኪፕሩቶ ተቀድሞ በሁለተኝነት ውድድሩን አጠናቁዋል።

በ1500ሜትር የሴቶች ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ተከታትለው በመግባት አስደናቂ ድል ተጎናጽፈዋል ።
ድርቤ ወልተጂ በሚገርም ብቃት 1ኛ ስትወጣ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3:59:19 ፈጅቶባታል በአንፃሩ አያል ዳኛቸው 66ሰከንዶችን ብቻ በመዘግየት በ(3:59:87) ሁለተኛ ለመውጣት ችላለች፤ ነፃነት ደስታ 3ተኛ መብሪት መኮንን ደግሞ 7ተኛ ሆነው በመጨረስ አስገራመመ ድል ተጎናጽፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.