ተጠባቂው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ።

▪️በስታድ ዴ ፍራንስ ስቴዲየም ተጠባቂው የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ተካሂዷል። ጨዋታው መጀመር ከነበረበት ሰአት ደጋፊዎች በጊዜ ወደ ስቴዲየም ባለመግባታቸው ምክንያት ዘግየት ብሎ ለመጀመር ተገዶ ነበር።

የመጀመሪያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥር እንዲሁም በኳስ ሙከራዎች ሊቨርፑል የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገዋል። 5 ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ማድረግ ችለዋል። ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ከሜዳው ለመውጣት ሲቸገር ተስተውሏል። የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው ካሪም ቤንዜማ ለቡድኑ ግብ ያስገኘ ቢሆንም ከጨዋታው ውጪ በመባል ተሽሮበታል።

▪️ሁለተኛው አጋማሽ  ሪያል ማድሪድ በአንፃራዊነት ከሜዳቸው በመውጣት ለማጥቃት ጥረት አድርገዋል። ጥረታቸውም ፍሬ አፍርቶ በ59ኛው ደቂቃ ላይ ከ ፌዴ ቫልቬርዴ የተሻገረውን ኳስ ቪኒሺየስ ጁኒየር በቀላሉ በማስቆጠር ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።

▪️ከዚህ ግብ በኋላ ሊቨርፑል በተደጋጋሚ የአቻነት ግብ ለማግኘት ሞክረዋል። የማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቱዋ ግን የሚቀመስ አልሆነም።

ውጤቱም 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን ሪያል ማድሪድ ለ14 ኛ ጊዜ ዋንጫውን በማሳካት በዚህ መድረክ እንከን የለሹ ፣ ምህረት የለሽ እንዲሁም አይበገሬው ቡድን እንደሆነ አስመስክሯል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲም 4 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን በማሳካት የመጀመሪያው አሰልጣኝ በመሆን አዲስ ታሪክ ሰርተዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.